የአፋር ተረቶች Here you can get Afar folktale
አፋር ተረቶች / Afar Folktals
አፋር
Afar
በዚህኛው ስብስብ ውስጥ ያሉ ተረቶች የተነገሩት በመጋቢት ወር 1989ዓ.ም. በተለያዩ ሁኔታዎች ሲሆን ይኸውም በክልሉ ባህል ቢሮና እንዲሁም በወቅቱ የቢሮው ሃላፊ በሆኑት በአቶ ሙሀመድ አህመድ አልጋኒ ቤት ውስጥ ነበር፡፡ ታሪኮቹ በሙሉ የተራኪዎቹ ባይሆኑም አብዛኛዎቹ በአፋርኛ ቋንቋ ተተርከው በሙሃመድ አልጋኒ ወደ አማርኛ የተተረጎሙ ናቸው፡፡ አማርኛውም ወደ እንግሊዘኛ የተተረጎመው በብሪትሽ ካውንስሉ ሰራተኛ በማይክል ዳንኤል አምባቸው ነው፡፡
Afar house near Assayita
በአሳይታ አካባቢ የሚገኝ የአፋር ቤት
አንዳንዶቹ የአፋር ተረቶች በሌላ የኢትዮጲያ ክልሎች ውስጥ ከሚነገሩት ተረቶች ጋር ተመሳሳይነት አላቸው (ለምሳሌ፣ ተንኮለኛው ቀበሮ እና ሶስቱ)፡፡ በአፋር ተረቶች ውስጥ ጎልቶ የሚታየው የእንቆቅልሽ ብሂል ነው (ለምሳሌ፣ አልጋ ወራሹ ልዑል) ፡፡ይህ በቅርብ ምስራቅ ሀገሮች የሚታየው ጥንታዊ የታሪክ አነጋገር ስልት ነው፡፡ (በብሉይ ኪዳን ውስጥ የሚገኘውን የሳምሶንን ታሪክ እና የኤዲፐስን አፈ-ታሪክ ማመሳከር ይቻላል፡፡)
ደስ ይላል
ReplyDelete