Posts

Showing posts from 2020

የአፋር ተረቶች Here you can get Afar folktale

Image
W3.CSS አፋር ተረቶች / Afar Folktals አፋር Afar በዚህኛው ስብስብ ውስጥ ያሉ ተረቶች የተነገሩት በመጋቢት ወር 1989ዓ.ም. በተለያዩ ሁኔታዎች ሲሆን ይኸውም በክልሉ ባህል ቢሮና እንዲሁም በወቅቱ የቢሮው ሃላፊ በሆኑት በአቶ ሙሀመድ አህመድ አልጋኒ ቤት ውስጥ ነበር፡፡ ታሪኮቹ በሙሉ የተራኪዎቹ ባይሆኑም አብዛኛዎቹ በአፋርኛ ቋንቋ ተተርከው በሙሃመድ አልጋኒ ወደ አማርኛ የተተረጎሙ ናቸው፡፡ አማርኛውም ወደ እንግሊዘኛ የተተረጎመው በብሪትሽ ካውንስሉ ሰራተኛ በማይክል ዳንኤል አምባቸው ነው፡፡ Afar house near Assayita በአሳይታ አካባቢ የሚገኝ የአፋር ቤት አንዳንዶቹ የአፋር ተረቶች በሌላ የኢትዮጲያ ክልሎች ውስጥ ከሚነገሩት ተረቶች ጋር ተመሳሳይነት አላቸው (ለምሳሌ፣ ተንኮለኛው ቀበሮ እና ሶስቱ)፡፡ በአፋር ተረቶች ውስጥ ጎልቶ የሚታየው የእንቆቅልሽ ብሂል ነው (ለምሳሌ፣ አልጋ ወራሹ ልዑል) ፡፡ይህ በቅርብ ምስራቅ ሀገሮች የሚታየው ጥንታዊ የታሪክ አነጋገር ስልት ነው፡፡ (በብሉይ ኪዳን ውስጥ የሚገኘውን የሳምሶንን ታሪክ እና የኤዲፐስን አፈ-ታሪክ ማመሳከር ይቻላል፡፡) በቅርቡ ሁሉም የአፋር ተረቶች ይለቀቃሉ እስከዛ comment like share pleas

የኢትዮጵያ ተረቶች

Image
[ Welcome To Ethiopian Tube ] አብዱል ራህማን አብዱላሂ - የተረት አባት ከሃረር በዚህ ድረ-ገጽ ላይ ከእያንዳንዱ የኢትዮጵያ ክፍል እኤአ ከ1997 እስከ 2001 ዓ.ም. የተሰበሰቡ ተረቶችን ያገኛሉ፡፡ ተረቶቹ በመጀመሪያ የተሰበሰቡት ቀለል ላለ የእንግሊዝኛ ንባብ መጽሃፍት ለማዘጋጀት ሲሆን ይህም ህጻናት ተማሪዎች በየክልላቸው ባህላዊ እሴቶች ላይ ተመስርተው የተጻፉትን ተረቶች ማንበብ እንዲችሉና በዚያውም የእንግሊዝኛ ቋንቋ ችሎታቸውን እንዲዳብሩ በማሰብ ነው፡፡ በአጠቃላይ እንደነዚህ ያሉ ስምንት የንባብ መጽሃፍት ተዘጋጅተዋል፡፡ ይህ ድረ-ገጽ የተዋቀረው በፕሮጀክቱ ሂደት ወቅት የተሰበሰቡትን የበለጸጉና ልዩ ልዩ ተረቶች ለሰፊው አንባቢ ተደራሽ ለማድረግ ነው፡፡ እነዚህ ተረቶች ከጥንት ጀምሮ ኢዮጵያውያን እርስ በርስ ሲተራረኩዋቸው የኖሩ ድንቅ ሃብቶች ሲሆኑ ብዙዎቹ ከዚህ በፊት በጽሁፍም ሆነ ወደ እንግሊዝኛ ቋንቋ ተተርጉመው የሚገኙ አይደሉም፡፡ ተረቶቹ የተሰበሰቡት በትምህርት ሚኒስቴርና በብሪቲሽ ካውንስል የበላይ ተቆጣጣሪነትና በኢትዮጵያ ክልላዊ የባህልና ትምህርት ቢሮዎች ተባባሪነት ኤልሳቤት ላየርድ በተባሉ ተረት አሰባሳቢ ነው፡፡ ሁሉም ተረቶች በእንግሊዝኛ ተጽፈው ይገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ብዙዎቹን ተረቶች በተለያዩ ሁኔታዎችና ባልተዋጣለት መሳሪያ በመስክ ላይ ተራኪዎቹ ሲተርኳቸው የተቀዳውን ኦሪጂናል ድምጽ ማዳመጥ ይችላሉ፡፡ አብዛኛዎቹ ተረቶች የተተረኩት በአማርኛ፣ ጥቂቶቹ ደግሞ በእንግሊዝኛ ቢሆንም ሌሎች በተለያዩ ቋንቋዎች ማለትም በኦሮምኛ፣በሶማሊኛ፣በአኙዋክ፣በጉሙዝና በኑዌር ቋንቋዎች የተተረኩም አሉ፡፡ ቅጂዎቹ የሚሰሙት በቅደም ተከተል ሲሆን አሁን ባሉበት ሁኔታ ቅጂዎቹን ከጽሁፎቻቸው ማዛመድ አልተቻለም፡፡ የተረ...

Welcome to this page

Your bouncing text goes here